top of page

ሰው ሰራሽ አስተውሎት እና አዳዲስ ፈጠራዎች

አዳዲስ ፈጠራዎች ጠንካራ የጤና ሥርዓትን ለመገንባት ጥቅም ላይ ማዋል

ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የጤና መረጃዎች የሚተነተኑበትን፣ የሚተረጎሙበትን እና ጥቅም ላይ የሚውሉበትን መንገድ እያዘመነ ይገኛል።  ከዚሁ ጋር ተያይዞ ሰው ሰራሽ አስተውሎት የበሽታዎችን ወረርሽኝ ከመተንበይ ጀምሮ በትልልቅ የመረጃ ስብስብ (datasets) ውስጥ ያሉ ሥርዓተ-ክስተቶችን (Patterns) እስከ መለየት ድረስ በጤና ሥርዓቱ ውስጥ ፈጣን፣ ትክክለኛ እና ይበልጥ ምላሽ ሰጪ የሆኑ ውሳኔዎችን ለመስጠት የሚያስችል ከፍተኛ አቅም አለው።

የኢትዮጵያ የመረጃ ትንተና እና ሞዴሊንግ መማክርት ሰው ሰራሽ አስተውሎት እና ሌሎች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች በኢትዮጵያ ውስጥ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን የጤና ችግሮችን ለመፍታት እንዴት ባለ ኃላፊነት እና ውጤታማነት ጥቅም ላይ ሊውሉ እንደሚችሉ በመመርመር ላይ ይገኛል።

መማክርቱ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ጠንካራ በሆኑ የመረጃ ሥርዓቶች፣ ዓውዱን ባገናዘበ የአስተዳደር ሥርዓት እና ባለቤትነቱ የኢትዮጵያ በሆነ መልኩ መመሥረት እንዳለባቸው ይገነዘባል። ሰው ሰራሽ አስተውሎት ጠቃሚ የሆነ ሥነ-ምህዳርን የፈጠረ ቢሆንም ውጤታማነቱ የሚወሰነው ግን ቴክኖሎጂው የተገነባበት የመረጃ ጥራት፣ የመረጃዎች ተደራሽነት እና ወካይነት ላይ ተመስርተ ነው። በሂደቱ የሚሰሩ ሥራዎች ሥነ-ምግባራዊ ጉዳዮችን ያሟሉ፣ ግልጽ እና ፍትሐዊ መሆናቸውን ማረጋገጥ የመማክርቱ የትኩረት መስክ ነው።

መማክርቱ በአብነታዊ (pilot) ፕሮጀክቶች፣ በቴክኒክ አጋርነት እና አቅምን በሚገነቡ ሌሎች ጥረቶች አማካኝነት ነባር አሰራሮችን ለማጠናከር እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት የላቀ የትንተና ዘርፍ ያለውን ሀገር አቀፍ ሙያ ለማጎልበት እገዛ እያደረገ ይገኛል። እነዚህ ቴክኖሎጂዎች ለፖሊሲና ለፕሮግራም ውሳኔ አሰጣጥ እንዴት አጋዥ መሆን እንደሚችሉ የሚያሳዩ ተግባራዊ አሰራሮችን (use cases) መፍጠር ይህን ሂደት ለመደገፍ ከሚተገበሩ ተግባራት መካከል ተጠቃሽ ነው፡፡

ሰውሰራሽአስተውሎትእናአዳዲስፈጠራዎችለሚከተሉትዓላማዎችጥቅምላይይውላሉ፡፡

​

  • የአሠራር ውጤታማነትን ለማሳደግና አሠራሮችን ለማዘመን፣

  • የሕክምና አገልግሎት ፍላጎቶችን አስቀድሞ ለመተንበይ፣

  • የሀብት ክፍፍልን ለማሻሻል፣

  • ለጤና ስጋት የተጋለጡ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ለመለየት፣

  • የበሽታዎችን ቅኝት (surveillance) ለማጠናከር፣

  • ይበልጥቀልጣፋየሆነየጤናሥርዓትእቅድንለመደገፍጥቅምላይይውላሉ፡፡

​

የኢትዮጵያ የመረጃ ትንተና እና ሞዴሊንግ መማክርት ሀገራዊ አቅምን በማጠናከርና አዳዲስ ፈጠራዎችን በማስፋፋት እነዚህ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ለተሻለ እና ይበልጥ ጠንካራ ለሆነ የጤና ሥርዓት ጉልህ አስተዋጽዖ እንዲያበረክቱ ማድረግን ዓላማው አድርጎ ይንቀሳቀሳል።

ChatGPT Image Jun 8, 2026, 05_35_52 PM.png

ያግኙን

ከመማክርቱ ቡድን ጋር ይገናኙ

ይሳተፉ

የወደፊቱ የኢትዮጵያን የጤና መረጃ ሥርዓት ለማቅናት የበኩልዎን ያበርክቱ፡፡

የምርምር ጥያቄ፣ የአባልነት ፍላጎት ወይም የትብብር ሃሳብ ካለዎት ያግኙን

bottom of page