top of page

የሥርዓተ-ፆታ እኩልነት እና አካታችነት

የጤና መረጃ ውጤታማ ለሆነ የውሳኔ አሰጣጥ አጋዥ ሊሆን የሚችለው የሁሉንም ሰዎች ልምድ፣ ፍላጎት እና ነባራዊ ሁኔታ ማንፀባረቅ ሲችል ነው። ሆኖም ግን አንዳንድ የሕብረተሰብ ክፍሎች በመረጃ አሰባሰብ፣ ትንተና እና ውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች ውስጥ በበቂ ሁኔታ አይወከሉም፡፡ በዚህ ምክንያት የጤና ሥርዓቱ በውስጡ ያሉበትን የውክልና ችግሮች እንዳይለይ እና የመፍትሔ እርምጃ እንዳይወስድ መሰል ችግሮች እንቅፋት ሆነውበታል።

የኢትዮጵያ የመረጃ ትንተና እና ሞዴሊንግ መማክርት በሀገር አቀፍ ደረጃ በጤና መረጃ፣ ትንተና፣ ሞዴሊንግ እና ሰው ሰራሽ አስተውሎት ዙሪያ ፍትሃዊና አካታች አሰራሮችን ለማጠናከር ቁርጠኛ ነው። መማክርቱ ጥራት ያለው እና ወካይ የሆነ ማስረጃ የማመንጨት እና የመጠቀምን ባህል በማሳደግ ፈጣን ምላሽ የሚሰጡ ፖሊሲዎችን፣ ጠንካራ ፕሮግራሞችን እና የተሻሉ የጤና ውጤቶችን ለሁሉም የሕብረተሰብ ክፍሎች ለማቅረብ አልሞ ይሰራል።

ፍትሃዊ እና ሥርዓተ-ፆታን ያገናዘቡ ማስረጃዎችን ማስፋፋት

ፆታ፣ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ እና ሌሎች ተያያዥ ሁኔታዎች የጤና ስጋቶች፣ የአገልግሎቶች ተደራሽነት እና የሕክምና ውጤቶች ላይ ተፅዕኖ አላቸው። ይህ በእንዲህ እያለ እነዚህ ጉዳዮች በጤና መረጃ ሥርዓት ውስጥ በበቂ ሁኔታ አይካተቱም።

​

የኢትዮጵያ የመረጃ ትንተና እና ሞዴሊንግ መማክርት ትኩረታቸውን እኩልነት እና ፆታ ላይ ያደረጉ የመረጃዎች አሰባሰቦች፣ ትንተናዎች እና አጠቃቀሞችን ለማጠናከር ከአባላቱ ጋር ይሰራል፡፡ ይህም በፆታ የተለዩ/የተደራጁ መረጃዎች አጠቃቀምን መደገፍ፣ የእኩልነት ጉዳዮችን በትንተና እና ሞዴሊንግ ሥራዎች ውስጥ ማካተትን፣ እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የጤና ተደራሽነት ችግሮችን እና የጤና አገልግሎቶች ላይ ያላቸውን ግንዛቤ ማሻሻልን ያካትታል። ሂደቱ የውክልና ችግሮችን እና አለመመጣጠኖችን የበለጠ ግልጽ በማድረግ ማስረጃዎች አካታች የሆኑ ፖሊሲዎችን እና ፕሮግራሞችን እንዲደግፉ እገዛ ያደርጋል፡፡

እኩልነትን ያማከለ የመረጃ ሥርዓትን ማጠናከር

እኩልነት የሚመሰረተው በሚሰበሰቡ መረጃዎች ዓይነት ላይ ብቻ ሳይሆን መረጃዎች በሚገኙበት፣ በሚተነተኑበት እና ጥቅም ላይ በሚውሉበት መንገድ ላይ ጭምር ነው። የኢትዮጵያ የመረጃ ትንተና እና ሞዴሊንግ መማክርት የመረጃ ጥራትን ለማሻሻል፣ ከሥነ-ሕዝብ እና ከእኩልነት ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ተደራሽነት ለማጠናከር፣ በመረጃ ሽፋን ላይ ያሉ ክፍተቶችን ለመቀነስ እና የትንተና መሣሪያዎችን እና የባለሙያዎችን ተደራሽነት ለማስፋፋት የሚደረጉ ጥረቶችን ይደግፋል። እነዚህ ጥረቶች ማስረጃዎች የኢትዮጵያን ሕዝብ ስብጥር የሚያንፀባርቁ እንዲሆኑ እና በሁሉም የጤና ሥርዓት እርከኖች የበለጠ አካታች የሆኑ ውሳኔዎችን እንዲወሰኑ ለመደገፍ ያግዛሉ።

የጤና መረጃ ላይ የሚሰማራ የሰው ኃይልን አካታች በሆነ መልኩ መገንባት

ዘላቂ የሆነ የጤና መረጃ ሥነ-ምህዳር የተለያዩ አመለካከቶችን የሚያስተናግድ እና አካታች የሆነ አመራርን ይፈልጋል። ሴቶች እንደ መረጃ ሳይንስ፣ ትንተና፣ ሞዴሊንግ እና ሰው ሰራሽ አስተውሎት ባሉ በርካታ የቴክኒክ ዘርፎች ውስጥ አሁንም በበቂ ሁኔታ አልተወከሉም።

​

የኢትዮጵያ የመረጃ ትንተና እና ሞዴሊንግ መማክርት ከመንግሥት፣ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ከምርምር ተቋማት ጋር በሚያደርጋቸው አጋርነቶች አማካኝነት የሥልጠና፣ የምክርና ድጋፍ ፣ የሙያ ክህሎት እና የአመራር ክህሎት ስልጠናዎችን ይደግፋል። መማክርቱ በተለይም በኢትዮጵያ የጤና መረጃ ማህበረሰብ ውስጥ የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ ልዩ ትኩረት ይሰጣል፡፡ ይህም ጠንካራ እና ብዘሃነትን ያማከለ የወደፊቱን የዘርፉን መሪዎች ለማፍራት ይረዳል።

​

እኩልነት እና አካታችነት በተናጠል የሚታዩ ጉዳዮች አይደሉም። በመሆኑም በመረጃ፣ በትንተና እና በፈጠራ ላይ የሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች ለሁሉም ሰው የበለጠ ፍትሐዊ የጤና ውጤቶችን እንዲያስገኙ በሁሉም የመማክርቱ የሥራ መስኮች ውስጥ ተካትተዋል።

Stockphotos-13_edited.jpg

ያግኙን

ከመማክርቱ ቡድን ጋር ይገናኙ

ይሳተፉ

የወደፊቱ የኢትዮጵያን የጤና መረጃ ሥርዓት ለማቅናት የበኩልዎን ያበርክቱ፡፡

የምርምር ጥያቄ፣ የአባልነት ፍላጎት ወይም የትብብር ሃሳብ ካለዎት ያግኙን

bottom of page