መረጃን ማዕከል ባደረጉ መንገዶች የተሻሉ ውሳኔዎችን መደገፍ
ትንተና እና ሞዴሊንግ በጤናው ዘርፍ ያሉ ስጋቶችን ለመረዳት፣ ወደፊት የሚከሰተውን ለመተንበይ እና የመፍትሔ እርምጃዎችን ውጤታማነት ለመገምገም የሚያገልግሉ መሣሪያዎች ናቸው። እነዚህ መሣሪያዎች ፖሊሲ አውጪዎችና የፕሮግራም መሪዎች ከተለመዱ አሃዛዊ ሪፖርቶች ተሻግረው በማስረጃ ላይ የተመሠረቱ የጠሩ ውሳኔዎችን እንዲወስኑ ያስችሏቸዋል።
የኢትዮጵያ የመረጃ ትንተና እና ሞዴሊንግ መማክርት በጤና ሚኒስቴር ቅድሚያ በሚሰጣቸው የጤና ዘርፎች (ችግሮች) ላይ የዳበሩ የትንተና እና የሞዴሊንግ ዘዴዎችን ለመተግበር እየሠራ ይገኛል። በዚህ ሂደት መማክርቱ ከመንግሥት፣ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና ከሌሎች አጋር ድርጅቶች የተውጣጡ ባለሙያዎችን በማስተባበር ለፖሊሲ፣ ለእቅድና ለፕሮግራም ትግበራ አጋዥ የሆኑ ጠንካራ ሥነ-ዘዴዎች እንዲዘጋጁ ድጋፍ ያደርጋል።
በኢትዮጵያ ውስጥ የሞዴሊንግ አጠቃቀም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል፡፡ በተለይም እንደ ወባ ቁጥጥር፣ የኮቪድ-19 ምላሽ፣ የጤና ሰው ሀብት እቅድ እና የሕክምና ግብአቶች ትንበያ ባሉ ዘርፎች ላይ ሰፊ ጥቅም ላይ ውሏል። ሆኖም ግን የዚህ ሥራ አብዛኛው ክፍል በውጭ ሀገር ባለሙያዎች ድጋፍ ከመከናወኑም በላይ አብዛኛውን ጊዜ ቅንጅት በጎደላቸውና በተበታተኑ መንገዶች የተካሄደ ነበር።
መማክርቱየሀገርውስጥባለሙያዎችንአቅምበማጎልበትእናበተቋማትመካከልትብብሮችንበማመቻቸትወጥናየተቀናጀሀገራዊአሠራርለመዘርጋትይሠራል፡፡በተጨማሪምበርካታየትንተናዘዴዎችጥቅምላይየሚውሉበትንመንገድበመቀየስከስታቲስቲክስትንተናእናትንበያጀምሮእስከየረቀቁየሂሳብናቀመራዊሞዴሊንጎችድረስአገልግሎትየሚሰጡበትንመንገድይደግፋል፡፡
በእነዚህ ዘዴዎች ምላሽ የሚያገኙ ጥያቄዎች፦
-
የበሽታዎች ስርጭት ሁኔታ በጊዜ ሂደት እንዴት ሊቀያየር እንደሚችል፣
-
የትኞቹ የሕክምናና የመከላከል እርምጃዎች ከፍተኛ ለውጥ ሊያመጡ እንደሚችሉ፣
-
የሀብት ክፍፍልን በተሻለና ውጤታማ መንገድ እንዴት ማከናወን እንደሚቻል
-
ለወደፊት የሚያስፈልጉ የሰው ሀብት እና የሕክምና ግብአቶች ፍላጎት ምን እንደሆነ፣
-
የጤና ሥርዓቶች በየጊዜው ለሚከሰቱ ችግሮች እንዴት ምላሽ መስጠት እንደሚችሉ የሚሉት ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ የመረጃ ትንተና እና ሞዴሊንግ መማክርት ሀገራዊ የሞዴሊንግ አቅምን በማጠናከር እና በማስረጃ ላይ የተመሠረተ የውሳኔ አሰጣጥ ባህልን በማስተዋወቅ ቀልጣፋ፣ ውጤታማና ፍትሐዊ የሆኑ የጤና ፕሮግራሞችን መደገፍን ዓላማው አድርጎ ይንቀሳቀሳል።
.png)