top of page

ከማስረጃ ወደ ፖሊሲ

በምርምር እና በውሳኔ አሰጣጥ መካከል ያለውን ክፍተት መሙላት

በዓለም አቀፍ ደረጃ የጤና ሥርዓቶች ላይ ከተደቀኑ ተግዳደሮቶች አንዱ የምርምር ግኝቶች፣ የትንተና ውጤቶችና የሞዴሊንግ ውጤቶች የሰዎችን ሕይወት ሊያሻሽሉ ወደሚችሉ ፖሊሲዎች፣ ፕሮግራሞች እና ኢንቨስትመንቶች መተርጎማቸውን ማረጋገጥ ነው።

ስለሆነም ማስረጃን ወደ ፖሊሲ መቀየር የመማክርቱ ዋና የሥራ መሠረት ነው።

የመማክርቱአባላትየማስረጃዝግጅትሂደትከነባራዊየውሳኔአሰጣጥፍላጎቶችጋርየተጣጣመመሆኑንለማረጋገጥፖሊሲአውጪዎችን፣የፕሮግራምመሪዎችን፣ተመራማሪዎችንእናየቴክኒክባለሙያዎችንበማካተትይሰራሉ፡፡

ይህም ቅድሚያ የሚሰጣቸውን የፖሊሲ ምርምር ጥያቄዎች የመለየት፣ በተመራማሪዎች እና በውሳኔ ሰጪዎች መካከል ውይይቶችን የማመቻቸት፣ የፖሊሲ መግለጫዎችን (policy briefs) ለውሳኔ አሰጣጥ ግብዓትነት የማዘጋጀት፣ እንዲሁም በዕቅድ እና በፕሮግራም ሂደቶች ውስጥ ማስረጃዎች መጠቀምን የማስፋፋት ሥራዎችን ያካትታል።

መማክርቱ ማስረጃዎች በተሻለ ሁኔታ ተፅዕኖ መፍጠር የሚችሉት ግልጽ እና ውጤታማ በሆነ መንገድ ሲተላለፉ እንደሆነ ይገነዘባል። ከዚህ አኳያ እውቀትን በማሸጋገር (knowledge translation) ፣ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ እና ለፖሊሲ ግብዓት የሆኑ ሥራዎችን በማዘጋጀት ሂደት ላይ መማክርቱ ከፍተኛ ትኩረት ይሰጣል።

በእነዚህ ጥረቶች አማካኝነት መማክርቱ በኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ ውስጥ በመረጃ ላይ የተመሠረተ የውሳኔ አሰጣጥ ባህልን ለማዳበርና እና በመረጃና በትንተና ላይ የሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች ትርጉም ያለው ተፅዕኖ ማምጣታቸውን ለማረጋገጥ አልሞ ይሰራል።

ChatGPT Image Jun 8, 2026, 05_35_52 PM.png

ያግኙን

ከመማክርቱ ቡድን ጋር ይገናኙ

ይሳተፉ

የወደፊቱ የኢትዮጵያን የጤና መረጃ ሥርዓት ለማቅናት የበኩልዎን ያበርክቱ፡፡

የምርምር ጥያቄ፣ የአባልነት ፍላጎት ወይም የትብብር ሃሳብ ካለዎት ያግኙን

bottom of page