የመጪውን ትውልድ የጤና መረጃ ሥርዓት መሪዎች ማፍራት
በጤና መረጃ ዘርፍ ዘላቂ የሆነ የሀገር ውስጥ አቅምን መገንባት የመማክርቱ ተልዕኮ ዋነኛ አካል ነው።
በመረጃ ሥርዓቶች፣ በመረጃ ትንተና እና በቴክኖሎጂ ላይ የሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች አስፈላጊ ቢሆኑም መሰል ተነሳሽነቶች ማስረጃዎችን ለማዘጋጀት እና ለመጠቀም አቅም ባላቸው አካላት ላይ ጥገኛ ናቸው፡፡ በዚህ መነሻነት የአቅም ግንባታ ጉዳይ በመማክርቱ በርካታ ስራዎች ውስጥ ተካትቶ ይገኛል፡፡
የኢትዮጵያ የመረጃ ትንተና እና ሞዴሊንግ መማክርት በጤና መረጃ ትንተና፣ በሞዴሊንግ፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት እና በማስረጃ ላይ የተመሠረተ ፖሊሲ ቀረፃ ዙሪያ ያለውን ክህሎት ለማጠናከር ከመንግሥት ተቋማት፣ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና ከምርምር ተቋማት ጋር በትብብር እየሰራ ይገኛል። በስልጠና፣ በምክርና ድጋፍ ፣ በፌሎውሺፕ እና በተቋማት አጋርነት አማካኝነት፣ መማክርቱ የሀገሪቱን ወቅታዊ የጤና ችግሮች መፍትሔ ለመስጠት የሚችሉ ኢትዮጵያውያን ተመራማሪዎችን፣ ተንታኞችን እና ፖሊሲ አውጪዎችን በብዛት ለማፍራት አልሞ እየሰራ ነው።
ከመማክርቱ ጋር በሚሰሩ በተለያዩ ተቋማት ውስጥ ነባራዊ አቅሞችና ፍላጎቶች ላይ የሚደረግ ግምገማና ዳሰሳ ተስማሚ የሆኑ የመማማሪያ ፍላጎቶችን ለማወቅ እና ዕድሎችን ለማመቻቸት መንገድ ይጠርጋል። እነዚህ እንቅስቃሴዎች የግለሰቦችንም ሆነ የተቋማትን አቅም ለማጠናከር የተነደፉ ዓውደ ጥናቶችን፣ ማስተርክላሶችን፣ የቴክኒክ ልውውጦችን፣ የምክርና ድጋፍ ፕሮግራሞችን እና ዓለም አቀፍ የትምህርት ዕድሎችን ያካትታሉ።
መማክርቱ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የትምህርት ስርዓት ዝግጅትን የሚደግፍ ሲሆን ይህም የወደፊቱ የጤና ባለሙያዎች በዘመናዊ የትንተና ዘዴዎች፣ በሞዴሊንግ ቴክኒኮች እና ፆታን ባገናዘቡ የመረጃ አጠቃቀም ባህሎች ላይ ስልጠና እንዲያገኙ ለማረጋገጥ ይረዳል።
በእነዚህ ኢንቨስትመንቶች አማካኝነት መማክርቱ የኢትዮጵያን የጤና መረጃ እና ትንተና አጀንዳ ለረጅም ዓመታት በበላይነት መምራት የሚችል ዘላቂ የሀገር ውስጥ የሰው ኃይል ለመገንባት አልሟል።
ኩነቶች እና የመማማሪያ መድረኮች
መማክርቱ በኢትዮጵያ የጤና መረጃ ሥነ- ምህዳር ውስጥ ትብብርን ለማጠናከር እና አቅምን ለመገንባት የተነደፉ ዓውደ ጥናቶችን፣ ሥልጠናዎችን፣ ቴክኒካዊ የልምድ ልውውጦችን እንዲሁም የትስስርና የትውውቅ ኩነቶችን አዘውትሮ ያዘጋጃል።
እያደገ ስላለው የመማክርቱ የሥራ ሂደቶች የበለጠ ለማወቅ መጪ ኩነቶችን፣ የስልጠና ዕድሎችን እና ባለፉት ጊዜያት የተከናወኑ ተግባራትን በሪፖርቶች ይመልከቱ።
.png)
